መጽሐፉ

አርነት በምርኮ ውስጥ ላሉት
አርነት በምርኮ ውስጥ ላሉት ከእስልምና ቀምበር ለመላቀቅ የሚያስችሉ ለየት ያሉ ሐሳቦችን ያቀርባል፡፡ እነዚህም ሰዎች እስልምናን ለቀው እንዲወጡ ሊረዷቸው ይችላሉ ወይንም ደግሞ ከእስልምና ዘንድ ከሚመጣባቸው ዛቻ የተነሳ ለሚሰቃዩቱ ፈውስ እና ነጻነትን ሊሰጡ ይችላሉ፡፡
መጽሐፉ ትክክለኛውን የሸሀዳ (የሙስሊሞች የእምነት መግለጫ) ትርጓሜ ይገልጣል እንዲሁም ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎች ለሙስሊም ላዕላይ አገዛዝ እጅ ለመስጠት የሚገቡትንም ውል (ዲማ) ይገልጣል፡፡ የነዚህ ሁለቱ ቃልኪዳኖች መንፈሳዊ ውርስ እንዴት እውን እንደሚሆን ለመግለጥ ደረጃ በደረጃ ያለውን ሂደት ያሳያል፡፡ ‘የእግዚአብሔርን ልጆች የከበረ ነጻነት’ ለመቀዳጀት (ሮሜ 8፡21) የመስቀሉን ኃይል መለማመድ የሚያስችሉ ተግባራዊ ቁልፎችን ይዟል፡፡
የተጠቀሱት ጸሎቶችና አዋጆች በስድስቱም አህጉራት በተግባር የተፈተኑ ናቸው፡፡ ሰዎችን ከእስራት ነፃ የማውጣት፣ ትውልድን የያዙትን ብርቱ ኃይላት የማስለቀቅ እንዲሁም ሰዎች የክርስቶስን የማዳን ኃይል ድፍረትን በተሞላ እና ውጤታማ በሆነ መንገድ መመስከር ይችሉ ዘንድ የማገዝ ፋይዳቸው የተረጋገጠ ነው፡፡
በአንገቴ ላይ የታሰረው ቀንበር ተፈቶ ተሰበረ ፡፡
ጸሎቶች ለነፃነት
ኢየሱስ ክርስቶስን ለመከተል የቁርጠኝነት ጸሎት
እስልምናን እንደገና ማደስ
የበላይነትን እንደገና ይንሱ
ማታለልን ያድሱ
ጸሎቱ እጅግ አስደናቂ ነው። እንደ ቀድሞ እንስሳ ይሰማኝ ነበር አሁን ግን ነፃ ወጥቻለሁ ፡፡
ከዲማማ ነፃነት ለማግኘት የሚደረግ ጸሎት
ለተያዙት ነፃነትን ለማወጅ የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው - ሉቃስ 4 18 ፡፡
ማስተማር ሀብቶች


































